ኢዮብ 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፤ የዝንጉ ሰውም ተስፋ ትጠፋለች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን የሚረሱ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ አምላክ የለሽ ኑሮ የሚኖሩም ሁሉ ተስፋቸው ትጠፋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፥ የአምላክ አልባ ሰውም ተስፋ ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን የሚረሱ ሰዎች ሁሉ ፍጻሜአቸው ልክ እንደዚሁ ነው፤ እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች ተስፋቸው ይቈረጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፥ የዝንጉም ሰው ተስፋ ይጠፋል። |
እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዐይኖቹም ወደ ድሃ ይመለከታሉ፤ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎችን ያዘ፤ እሳት እንደሚነድድ የሚነግራችሁ ማን ነው? የዘለዓለም ሀገርንስ የሚነግራችሁ ማን ነው?
አንቺ ግን ሰማያትን የፈጠረውን፥ ምድርንም የመሠረታትን ፈጣሪሽን እግዚአብሔርን ረስተሻል፤ ያጠፋሽ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሻል፤ ይቈጣሽ ዘንድ መክሮአልና፤ አሁን የሚያስጨንቅሽ ቍጣው የት አለ?
“ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን፥ ሥርዐቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤
አምላክህንም እግዚአብሔርን ፈጽሞ ብትረሳ፥ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል፥ ብታመልካቸውም፥ ብትሰግድላቸውም፥ ፈጽሞ እንደምትጠፋ እኔ ዛሬውኑ ሰማይንና ምድርን አስመሰክርብሃለሁ።