ኢዮብ 6:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቴማናውያንን መንገዶች፥ የሳባውያንን ክፋትና ቸልተኝነት ተመልከቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቴማን ነጋዴዎች ውሃ ይፈልጋሉ፤ የሳባ መንገደኞችም ተስፋ ያደርጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቴማን ነጋዴዎች ተመለከቱ፥ የሳባ መንገደኞችም ተጠባበቁአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቴማ መንገደኞች ውሃ ይፈልጋሉ፤ የሳባ ነጋዴዎችም ውሃ ለማግኘት ተስፋ ያደርጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቴማን ነጋዴዎች ተመለከቱ፥ የሳባ መንገደኞችም ተጠባበቁአቸው። |
የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ስም፥ የእግዚአብሔርንም ስም በሰማች ጊዜ ሰሎሞንን በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች።
ማራኪዎችም መጥተው ወሰዱአቸው፥ ብላቴኖችህንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም ብቻዬን አምልጬ እነግርህ ዘንድ መጣሁ” አለው።
ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየሀገራቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ንጉሥ ኤልፋዝ፥ አውኬናዊው መስፍን በልዳዶስ፥ አሜናዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊጐበኙትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ መጡ።