ኢዮብ 5:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜ ቤትህ በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ፤ ከንብረትህም አንዳች አይጐድልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንኳንህ በሚያስተማምን ሁኔታ እንዳለ ታውቃለህ፤ በረትህን ትቃኛለህ፤ አንዳችም አይጐድልብህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንኳንህ ሰላምን እንደሚያገኝም ታውቃለህ፥ በረትህን ትጐበኛለህ፥ አንዳችም አይጐድልብህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንኳንህ ሰላም እንደሚሰፍን ታረጋግጣለህ፤ የበጎችህንም በረት ስትጐበኝ ሁሉን በደኅና ታገኛቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንኳንህም በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ፥ በረትህን ትጐበኛለህ አንዳችም አይጐድልብህም። |
ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም በላቸው፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተገለጠልኝ፦ መጐብኘትን ጐበኘኋችሁ፤ በግብፅም የሚደረግባችሁን አየሁ፤
ዳዊትና ሰዎቹም ወደ ከተማ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በእሳት ተቃጥላ፥ ሚስቶቻቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም ተማርከው አገኙ።