La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ አንተ ብዙ​ዎ​ችን ታስ​ተ​ምር ነበር፥ የደ​ከ​ሙ​ት​ንም እጆች ታበ​ረታ ነበር፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ አንተ ብዙዎችን ታስተምር እንደ ነበር ዐስብ፤ የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ አንተ ብዙዎችን ታስተምር ነበር፥ የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ብዙ ሰዎችን አስተምረሃል፤ የደከሙትንም እጆች አበርትተሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ አንተ ብዙዎችን ታስተምር ነበር፥ የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፥

Ver Capítulo



ኢዮብ 4:3
21 Referencias Cruzadas  

ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት እጃ​ቸ​ውን ያጸና ዘንድ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ልብ ወደ እነ​ርሱ መል​ሶ​አ​ልና የቂ​ጣ​ውን በዓል ሰባት ቀን በደ​ስታ አደ​ረጉ።


እኔም ነገ​ርን እነ​ግ​ራ​ችሁ ነበር፤ ራሴ​ንም በእ​ና​ንተ ላይ እነ​ቀ​ንቅ ነበር።


የሰ​ማ​ች​ኝም ጆሮ ብፁዕ አለ​ችኝ፥ ያየ​ች​ኝም ዐይን ገለል አለች፤


ለዕ​ው​ራን ዐይን፥ ለአ​ን​ካ​ሳ​ዎ​ችም እግር ነበ​ርሁ።


ለድ​ሃ​ዎች አባት ነበ​ርሁ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ሰው ክር​ክር መረ​መ​ርሁ።


“ሰዎች እኔን ይሰ​ሙ​ኛል፥ ያዳ​ም​ጡ​ኝ​ማል፥ በም​ክ​ሬም ዝም ይላሉ።


በቃ​ልህ በሽ​ተ​ኞ​ችን ታስ​ነሣ ነበር፥ የሚ​ብ​ረ​ከ​ረ​ከ​ው​ንም ጕል​በት ታጸና ነበር።


የጻድቃን ከንፈሮች የሩቁን ያውቃሉ፤ ሰነፎች ግን በድህነት ይሞታሉ።


የጠቢባን ከንፈሮች በዕውቀት የታሰሩ ናቸው፤ የሰነፎች ልብ ግን የጸና አይደለም።


ጠቢብን ሰዎች ዐዋቂ ይሉታል፥ ነገሩም ጣፋጭ የሆነውን እጅግ ያደምጡታል።


ደካ​ሞች እጆ​ችና አን​ካ​ሶች ጕል​በ​ቶች፥ ጽኑ።


የም​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በብ ምላ​ስን ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነ​ቃ​ኛል፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን ሰጥ​ቶ​ኛል።


እኔም ያል​መ​ለ​ስ​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን ልብ ወደ ዐመፃ መል​ሳ​ች​ኋ​ልና፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መን​ገድ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውን እጅ አበ​ር​ት​ታ​ች​ኋ​ልና፤


በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም፦ ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ።


እኔ ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ደ​ክም ስለ እና​ንተ ጸለ​ይሁ፤ አን​ተም ተመ​ል​ሰህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አጽ​ና​ቸው።”


የሚ​ያ​በ​ረ​ታ​ታው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ታየው።


የሚ​ሰ​ሙ​አ​ችሁ ሞገ​ስን ያገኙ ዘንድ፥ ግዳ​ጃ​ችሁ እን​ዲ​ፈ​ጸም መል​ካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ።


ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻ​ገ​ራ​ልና፥ አን​ተም የም​ታ​ያ​ትን ምድር እርሱ ያወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ልና ኢያ​ሱን እዘ​ዘው፤ አደ​ፋ​ፍ​ረ​ውም፥ አጽ​ና​ውም።


ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​መ​ልሱ ታውቁ ዘንድ ንግ​ግ​ራ​ችሁ ሁል​ጊዜ በጨው እንደ ተቀ​መመ በጸጋ ይሁን።


ስለ​ዚ​ህም የላ​ሉ​ትን እጆች፥ የሰ​ለ​ሉ​ት​ንም ጕል​በ​ቶች አቅኑ።