ኢዮብ 39:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕንቍላልን በመሬት ላይ ትጥላለች፥ በአፈርም ውስጥ ታሞቀዋለች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕንቍላሏን መሬት ላይ ትጥላለች፤ እንዲሞቅም በአሸዋ ውስጥ ትተወዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንቁላልዋን በመሬት ላይ ትተዋለች፥ በአፈርም ውስጥ ታሞቀዋለች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰጎን እንቊላልዋን በምድር ላይ ትጥላለች፤ በዐፈር ላይ ተቀምጦም እንዲሞቅ ታደርጋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንቍላልዋን በመሬት ላይ ትተዋለች፥ በአፈርም ውስጥ ታሞቀዋለች፥ |
ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፤ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም የተረፈውን ጣዖታትን አበጅቶ ይሰግድላቸዋል።
ጋሜል። አራዊት እንኳ ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፤ የወገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኞች ሆኑ።