ኢሳይያስ 44:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፤ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም የተረፈውን ጣዖታትን አበጅቶ ይሰግድላቸዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ሰው ለማገዶ ይጠቀምበታል፤ ከዚያም ጥቂት ወስዶ በማንደድ ይሞቀዋል፤ እንጀራም ይጋግርበታል። ከዚሁ ጠርቦ አምላክ ያበጃል፤ ያመልከዋል፤ ጣዖትን ይሠራል፤ ወድቆም ይሰግድለታል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፤ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ሰው ከአንድ ዛፍ ግማሹን ለማገዶ፥ ግማሹንም ጣዖት ለመሥራት ይጠቀምበታል፤ ግማሹን እሳት አንድዶ ለመሞቅና እንጀራ ለመጋገር ይጠቀምበታል፤ በሌላው ጒማጅ ጣዖት ሠርቶ በፊቱ እየሰገደ ያመልከዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፥ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፥ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፥ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። Ver Capítulo |