የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
ኢዮብ 38:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም መልስልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስኪ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እኔ ልጠይቅህ፣ አንተም መልስልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ እንደ ጎበዝ ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ታሳውቀኛለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስቲ በፊቴ እንደ ወንድ ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም መልስልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ። |
የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
ጥንቱን ዕውቀትንና ምክርን የሚያስተምር እግዚአብሔር አይደለምን? በነፍሰ ገዳዩስ የሚፈርድ እርሱ አይደለምን?
“በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”
ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ ተጫምታችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ ይዛችሁ እንዲህ ብሉት፦ እየቸኰላችሁም ትበሉታላችሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነውና።
አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥም፤ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ። በፊታቸውም አትደንግጥ አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ይላል እግዚአብሔር።