ጆሮ ቃልን ትለያለችና፥ ጕሮሮም የመብልን ጣዕም ይለያል።
ምላስ ምግብን አጣጥሞ እንደሚለይ፣ ጆሮም የንግግርን ለዛ ለይቶ ያውቃል።
ምላስ መብልን እንደሚያጣጥም፥ ጆሮም ቃላትን ይለያልና።
የምግብ ጣዕም በምላስ እንደሚታወቅ፥ ንግግርም በጆሮ ይለያል።
ትናጋ መብልን እንደሚቀምስ፥ ጆሮ ቃልን ትለያለችና።
ዦሮ ነገርን የሚለይ አይደለምን? ጕረሮስ መብልን የሚቀምስ አይደለምን?
ጆሮዬ መርገሜን ትስማ፤ በወገኔም መካከል ክፉ ስም ይውጣልኝ።
እነሆ፥ አፌን ከፍቻለሁ፥ አንደበቴም ይናገራል።
“እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሌን ስሙ፤ እናንተም ዐዋቂዎች፥ መልካም ነገርን አድምጡ።
ፍርድን ለራሳችን እንምረጥ፤ በመካከላችንም ምን እንደሚሻል እንወቅ።
በአንደበቴ በደል የለምና አፌ ጕሮሮዬም ጥበብን ይናገራል።
መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል፤ እርሱን ግን የሚመረምረው የለም።
ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉዉን ለመለየት በሥራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው።