እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከደድሆ ዛፍ በታች ተቀመጠና፦ ይበቃኛል፤ አሁንም አቤቱ! እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ” ብሎ እንዲሞት ለመነ።
ኢዮብ 30:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እየዞሩ የሚለምኑና የሚበሉ በቅልውጥም የሚኖሩ ወራዶች፥ ዐመፀኞችና ከበጎ ነገሮች ሁሉ የተቸገሩ ናቸው። ከታላቅ ረኃብም የተነሣ ጨው ጨው የሚለውን የእንጨት ሥር ይበላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቍጥቋጦ ምድር ጨው ጨው የሚል አትክልት ለቀሙ፤ ምግባቸውም የክትክታ ሥር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቁጥቋጦ አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚለውን ቅጠላ ቅጠል ይቀጥፋሉ፥ እንዲሞቃቸውም የክትክታ ሥር ይበላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጨው ጨው የሚሉ የበረሓ ቅጠላ ቅጠሎችን ይለቅሙ ነበር፤ ጣዕም የሌላቸውንም የክትክታ ሥሮች ይበሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቍጥቋጦ አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚለውን አትክልት ይለቅማሉ፥ የክትክታ ሥር ደግሞ መብላቸው ነው። |
እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከደድሆ ዛፍ በታች ተቀመጠና፦ ይበቃኛል፤ አሁንም አቤቱ! እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ” ብሎ እንዲሞት ለመነ።