ኢዮብ 30:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀይሉ ቀኝ ተነሣብኝ፤ እግሮቹንም ዘረጋብኝ፤ የሞትንም መንገድ በእኔ ላይ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቀኜ በኩል ባለጌዎች ሆ! ብለው ተነሡብኝ፤ ለእግሬም ወጥመድ ዘረጉ፤ የዐፈር ድልድልም አዘጋጁብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥ እግሬንም ያሰናክላሉ፥ የጥፋታቸውን መንገዶች በእኔ ላይ ይቀይሳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስተቀኜ በኩል ስድ ዐደጎች ተነሡብኝ፤ እግሬንም ለማሰናከል ወጥመድ አጠመዱ፤ በእኔም ላይ ከበባ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥ እግሬንም ይገለብጣሉ፥ የጥፋታቸውን መንገድ በእኔ ላይ ይጐድባሉ። |
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባልንጀራው ላይ ይገፋፋል፤ ብላቴናውም በሽማግሌው ላይ፥ የተጠቃውም በከበርቴው ላይ ይታበያል።