ኢዮብ 30:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀስቱን አፎት ከፍቶ ክፉ አደረገብኝ፤ በፊቴም ልጓሙን ሰደደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ የቀስቴን አውታር ስላላላውና በመከራም ስለ መታኝ፣ በፊቴ መቈጠብን ትተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀስቴን አውታር አላልቶብኛል፥ አዋርዶኝማል፥ እነርሱም በፊቴ ልጓማቸውን ፈትተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኀይሌን አድክሞ ስላዋረደኝ፥ እነርሱ ልጓሙ እንደ ወለቀለት ፈረስ እንዳሻቸው ፈነጩብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀስቴን አውታር አላልቶብኛል፥ አዋርዶኝማል፥ እነርሱም በፊቴ ልጓማቸውን ፈትተዋል። |
በሙላት ወጣሁ፥ እግዚአብሔርም ወደ ቤቴ ባዶዬን መለሰኝ፣ እግዚአብሔር አዋርዶኛልና፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስጨንቆኛልና ኑኃሚን ለምን ትሉኛላችሁ? አለቻቸው።