ኢዮብ 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታናሹና ታላቁ በዚያ አሉ፤ ጌታውን ያገለገለ ባሪያም በዚያ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትንሹም ትልቁም በዚያ ይገኛል፤ ባሪያው ከጌታው ነጻ ወጥቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታናሽና ታላቅ በዚያ አሉ፥ አገልጋይም ከጌታው ነጻ ወጥቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታናናሽና ታላላቅ ሰዎች በአንድነት ይገኛሉ፤ ባሪያዎችም በዚያ ከጌቶቻቸው ነጻ ይወጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታናሽና ታላቅ በዚያ አሉ፥ ባሪያም ከጌታው ነጻ ወጥቶአል። |
ከፍ ያለውን ተመልክተው ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፤ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፍሬም ሳይበተን፤ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤቱ ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፤
አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ በሥጋም በነበረበት ጊዜ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይሰጥ ፈጣሪህን አስብ።
መንፈስን ለማስቀረት በመንፈሱ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞትም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በጦርነትም ጊዜ ስንብት የለም፥ ኀጢአትም ሠሪውን አያድነውም።