ኢዮብ 27:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ የኀጢአተኛ እድል ፋንታ ናት፥ ግፈኞችም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበሏት ሀብት ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ለክፉው ሰው የመደበው ዕድል ፈንታ፣ ግፈኛም ሁሉን ቻይ አምላክ የሚቀበለው ቅርስ ይህ ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ የበደለኛ እድል ፈንታ ከእግዚአብሔር ዘንድ፥ ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበላት ርስት ይህችው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ ሁሉን የሚችል አምላክ ክፉ ሰውንና ግፈኛን የሚቀጣው በዚህ ዐይነት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ እድል ፈንታ፥ ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበላት ርስት ናት፥ |
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤