Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 27:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “እነሆ ሁሉን የሚችል አምላክ ክፉ ሰውንና ግፈኛን የሚቀጣው በዚህ ዐይነት ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “እግዚአብሔር ለክፉው ሰው የመደበው ዕድል ፈንታ፣ ግፈኛም ሁሉን ቻይ አምላክ የሚቀበለው ቅርስ ይህ ነው፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “እነሆ የበደለኛ እድል ፈንታ ከእግዚአብሔር ዘንድ፥ ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበላት ርስት ይህችው፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ይህች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ተኛ እድል ፋንታ ናት፥ ግፈ​ኞ​ችም ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ዘንድ የሚ​ቀ​በ​ሏት ሀብት ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ እድል ፈንታ፥ ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበላት ርስት ናት፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 27:13
13 Referencias Cruzadas  

እናንተም እኮ ይህን ሁሉ ታውቃላችሁ፤ ታዲያ ይህን ከንቱ ነገር ለምን ትናገራላችሁ?”


“ከላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተወሰነው የሰው ዕድል ፈንታ ምንድን ነው? በአርያም ካለው ሁሉን ከሚችል አምላክ፥ የተሰጠው ድርሻስ ምንድን ነው?


በክፉ ሰው ላይ መዓት፥ በበደለኛ ሰውም ላይ ጥፋት፥ የታወቀ አይደለምን?


በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል፤ የሚጋረፍ ነፋስም የእነርሱ ዕድል ፈንታ ነው።


እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።


ክፉ ሰዎች ግን ምንም ነገር አይሰምርላቸውም፤ እግዚአብሔርንም ስለማይፈሩ ሕይወታቸው እንደ ጥላ ያልፋል፤


ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።


እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos