ኢዮብ 26:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃን ከጨለማ እስከሚለይበት ዳርቻ ድረስ፥ የውኃውን ፊት በተወሰነ ትእዛዙ ከበበው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለብርሃንና ለጨለማ ድንበር ይሆን ዘንድ፣ በውሆች ላይ የአድማስ ክበብ አበጀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃንና ጨለማ እስከሚለያዩበት ዳርቻ ድረስ፥ በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አሰመረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርሃንና ጨለማን ለመለየት በውቅያኖስ ፊት አድማስን ድንበር አድርጎ ዘረጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃንና ጨለማ እስከሚለያዩበት ዳርቻ ድረስ፥ በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አደረገ። |
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢትረፈረፍና ቢጮኽ ከእርሱ አያልፍም።