ኢዮብ 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙዎችን የተራቈቱትንም ያለ ልብስ ያሳድሩአቸዋል። መጐናጸፊያቸውንም ይገፍፏቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕራቍታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፤ በብርድም ጊዜ የሚለብሱት የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራቁታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፥ በብርድ ጊዜ የሚደረብ የላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሊቱን ሙሉ ራቁታቸውን ተኝተው ያድራሉ፤ ብርድ የሚከላከሉበትም ልብስ የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራቁታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፥ በብርድ ጊዜ መጐናጸፊያ የላቸውም። |
“የራሳቸው ያልሆነውን እርሻ ያለ ሰዓቱ ያጭዳሉ። ኃጥኣን ድሆችን በወይናቸው ቦታ ያለ ዋጋና ያለ ቀለብ ያሠሩአቸዋል።
ለተራበውም እንጀራህን አጥግበው፤ ድሆችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፤ የተራቈተውንም ብታይ አልብሰው፤ ከሥጋ ዘመድህ አትሸሽግ።
በይሁዳ፥ በሰማርያና በገሊላ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ጸንተው ኖሩ፤ ሕዝቡም በመንፈስ ቅዱስ አጽናኝነት በዙ።