ኢዮብ 24:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የራሳቸው ያልሆነውን እርሻ ያለ ሰዓቱ ያጭዳሉ። ኃጥኣን ድሆችን በወይናቸው ቦታ ያለ ዋጋና ያለ ቀለብ ያሠሩአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሜዳ መኖ ይሰበስባሉ፤ ከክፉዎች የወይን ቦታም ይቃርማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚያ በእርሻ ውስጥ እህላቸውን ያጭዳሉ፥ የበደለኛውንም ወይን ይቃርማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተቀጥረውም የሌላ ሰው መከር ሰብሳቢ ይሆናሉ፤ የክፉ ሰው ንብረት በሆነ የወይን አትክልት ቦታ ይቃርማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያ በእርሻ ውስጥ እህላቸውን ያጭዳሉ፥ የበደለኛውንም ወይን ይቃርማሉ። |
እነሆ፥ በምድረ በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች ሆኑ። ስለ እኔም ሥራቸውን ትተው ይወጣሉ፤ መብል፦ ከልጅነታቸው ጀምሮ ይጥማቸዋል።
ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፥ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፥ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም።
የምድርህን ፍሬ፥ ድካምህንም ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል፤ አንተም ሁልጊዜ የተጨነቅህ፥ የተገፋህም ትሆናለህ።
እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬ፥ የምድርህንም ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ እህልህን፥ ወይንህንም፥ ዘይትህንም፥ የላምህንና የበግህንም መንጋ አይተውልህም።