ኢዮብ 24:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ችግረኞችን በደሉአቸው፥ ጣሉአቸውም፤ ከተራቡትም የሚጐርሱትን ነጠቋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕራቍታቸውን ያለ ልብስ ይሄዳሉ፤ ነዶ ይሸከማሉ፤ ግን ይራባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያለ ልብስ ራቁታቸውን ይሄዳሉ፥ ተርበው ነዶዎችን ይሸከማሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድኾች ምንም ልብስ ሳይኖራቸው ራቁታቸውን ወደ ሥራ ይሰማራሉ። በመከር ወራት ነዶ ተሸክመው እያጋዙ እነርሱ ይራባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያለ ልብስ ራቁታቸውን ይሄዳሉ፥ ተርበው ነዶዎችን ይሸከማሉ፥ |
“የእርሻህን መከር ባጨድህ ጊዜ ነዶም ረስተህ በእርሻህ ብታስቀር፥ ትወስደው ዘንድ አትመለስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ፥ ለመጻተኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመበለትም ተወው።