ኢዮብ 22:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጹሕን ሰው ያድነዋል፤ በእጅህም ንጽሕና ትድናለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጎ ያልሆነውን ሰው እንኳ፣ ከአንተ እጅ ንጽሕና የተነሣ ያድነዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጹሑን ሰው ያድነዋል፥ በእጅህም ንጽሕና ትድናለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም ቅን ልብ ያለህ ብትሆን እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ እጆችህም ከበደል ሥራ የነጹ ቢሆኑ እግዚአብሔር ይታደግሃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጹሑን ሰው ያድነዋል፥ በእጅህም ንጽሕና ትድናለህ። |
ቴማናዊውም ኤልፋዝ፥ አውኬናዊው በልዳዶስና፥ አሜናዊው ሶፋር ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ስለ ኢዮብም ሲል ኀጢአታቸውን ይቅር አላቸው።
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
ከድሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎችህ ይሠራሉ፤ መሠረትህም ለልጅ ልጅ ዘመን ይሆናል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድንም አዳሽ ትባላለህ።
“በኢየሩሳሌም መንገዶች ሩጡ፤ ተመልከቱም፤ ዕወቁም፤ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደ ሆነ ይቅር እላቸዋለሁ ይላል እግዚአብሔር።
አሁንም ጸጋን ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ፣ ይህ ከእጃችሁ የተሰጠ ሲሆን ከቶ ፊታችሁን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘ጳውሎስ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ ከአንተም ጋር የሚሄዱትን ሁሉ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለአንተ ሰጥቶሃል።’