ኢዮብ 21:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ምን ኀጢኣተኞች በሕይወት ይኖራሉ? በባለጠግነትስ ስለ ምን ያረጃሉ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአተኞች ለምን በሕይወት ይኖራሉ? ለምን ለእርጅና ይበቃሉ? ለምንስ እያየሉ ይሄዳሉ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለምን ክፉዎች በሕይወት ይኖራሉ? ስለ ምንስ ያረጃሉ? ኃይላቸውንስ ስለምን ያጠነክራሉ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ክፉ ሰዎች ዕድሜአቸው ረዝሞ፥ ሃብታቸው በዝቶ በምድር ላይ ስለምን ይኖራሉ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምን ኃጢአተኞች በሕይወት ይኖራሉ? ስለ ምንስ ያረጃሉ? በባለጠግነትስ ስለ ምን ይበረታሉ? |
ከፀሓይ በታች በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኃጥኣን የሚደረገው ሥራ የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው ሥራ የሚደርስላቸው ኃጥኣን አሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።
ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፣ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለምን ዝም ትላለህ?