ኢዮብ 20:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈጽሞ ራሱን መርዳት አይችልም። የእፉኝትም መርዝ ከከንፈሩ በታች አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምግቡ በሆዱ ውስጥ ይመርራል፤ በውስጡም እንደ እባብ መርዝ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፥ እንደ እፉኝትም ሐሞት በውስጡ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሆዱ ውስጥ ግን ወደ መራራነት ይለወጣል፤ እንደ እባብ መርዝም ይሆንበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፥ እንደ እፉኝትም ሐሞት በውስጡ ይሆናል። |
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድዳባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፣ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።
በራብ ያልቃሉ፤ ለሰማይ ወፎችም መብል ይሆናሉ፤ ኀይላቸውም ይደክማል፥ ከምድር ይጠፉ ዘንድ የምድር አራዊትን ጥርስ፥ ከመርዝ ጋር እልክባቸዋለሁ።