ኢዮብ 17:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዘመኖች በጩኸት አለቁ፤ የልቤ ሥርም ተቈረጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜዬ ዐለቀ፤ ዕቅዴም ከሸፈ፤ የልቤም ሐሳብ ከንቱ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀኖቼ አለፉ፥ ዕቅዴና የልቤ ምኞት ቀለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የዕድሜዬ ዘመን ተፈጽሞአል፤ ዕቅዴና የልቤ ምኞት ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕድሜዬ አለፈች፥ አሳቤና የልቤ መሣርያ ተቈረጠ። |
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
ምክርን ብትመክሩም እግዚአብሔር ምክራችሁን ይለውጣል፤ የተናገራችሁትም ነገር አይሆንላችሁም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ፥ በሌሎች አሕዛብ እንደ ሆነ በእናንተም ዋጋዬን አገኝ ዘንድ ሁልጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንደ ወደድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረስም እንደ ተሳነኝ ልታውቁ እወድዳለሁ።