ኢዮብ 17:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እናንተ ሁሉ ወደዚህ መጥታችሁ ታዩኛላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ እውነትን አላገኘሁምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን እናንተ ሁላችሁ፣ እስኪ ተመልሳችሁ እንደ ገና ሞክሩ! ከመካከላችሁ አንድም ጠቢብ አላገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እናንተ ሁሉ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ፥ በእናንተም ዘንድ ጠቢብ አላገኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁላችሁም እንደገና መጥታችሁ በፊቴ ብትከራከሩ ከመካከላችሁ አንድ እንኳ አስተዋይ ሰው አላገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እናንተ ሁሉ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ፥ በእናንተም ዘንድ ብልሃተኛ አላገኝም። |
እግዚአብሔርም ይህን ቃል ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ እግዚአብሔር ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፥ “እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ አንዲት ቅን ነገርን በፊቴ አልተናገራችሁምና አንተና ሁለቱ ባልንጀሮችህ በድላችኋል።
እንግዲህ ጥበበኛ ማን ነው? ጸሓፊስ ማን ነው? ይህን ዓለምስ የሚመረምረው ማን ነው? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ስንፍና አላደረገውምን?
ይህንም የምላችሁ ስዘልፋችሁ ነው፤ እንግዲህ ከመካከላቸሁ ወንድማማቾችን ከወንድሞቻቸው ጋር ማስታረቅ የሚችል ሽማግሌ የለምን?