ኢዮብ 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ግን የዕብድ ቍርጥራጭና ብጥስጣሽ አደረግኸኝ፤ እኔንም መያዝህ ምስክር ሆነችብኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጨማተሬ ይመሰክርብኛል፥ ክሳቴም ተነሥቶብኛል፥ በፊቴም ይመሰክርብኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰውነቴ መጨማደድ ማስረጃ ሆኖብኛል፤ ክሳቴም በእኔ ላይ ተነሥቶ ኃጢአተኛ ነህ ብሎ ይመሰክርብኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጨማተሬ ይመሰክርብኛል፥ ክሳቴም ተነሥቶብኛል፥ በፊቴም ይመሰክርብኛል። |
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በክብርህ ላይ ውርደትን፥ በጌጥህ ላይም የሚነድና የሚያቃጥል እሳትን ይሰድዳል።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ የጻድቁን ድንቅ ተስፋ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እነርሱ ግን፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚያፈርሱ ወንጀለኞች ወዮላቸው!” አሉ።
የነጻችና የተቀደሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላይዋ እድፈት ወይም ርኵሰት እንዳያገኝባት፥ ቤተ ክርስቲያኑን ለእርሱ የከበረች ያደርጋት ዘንድ፤
በሙላት ወጣሁ፥ እግዚአብሔርም ወደ ቤቴ ባዶዬን መለሰኝ፣ እግዚአብሔር አዋርዶኛልና፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስጨንቆኛልና ኑኃሚን ለምን ትሉኛላችሁ? አለቻቸው።