እኔ ብናገር ቍስሌ አይድንም፤ ዝም ብልም ሕማሜ ይብስብኛል።
እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ አድክመኸኛል፤ ወገኖቼንም ሁሉ አጥፍተሃል።
አሁን ግን አድክሞኛል፥ ወገኔንም ሁሉ አፍርሰሃል።
አምላክ ሆይ! ከሰውነት ውጪ አደረግኸኝ፤ ቤተሰቤንም ሁሉ አጠፋህብኝ።
“ነፍሴ ስለ ተጨነቀች ቃሌን በእንጕርጕሮ አሰማለሁ፤ ነፍሴም እየተጨነቀች በምሬት እናገራለሁ።
“አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ የሚያውቅልኝም በአርያም ነው።
“ወንድሞች ተለዩኝ፥ ከእኔ ይልቅ ባዕዳንን ወደዱ። ጓደኞችም አላዘኑልኝም።
ኃጥኣን በዚያ በቍጣው መቅሠፍት ይቃጠላሉ፤ በዚያም በሥጋቸው የተጨነቁት ያርፋሉ።
በእርሱ የታመንሁ አይደለሁምን? ረድኤቱ ከእኔ ለምን ራቀ?
እንድታገሥ ለዘለዓለም እኖራለሁን? ሕይወቴ ከንቱ ነውና ከእኔ ራቅ።
እንዲሁ እኔ የከንቱ ወራትን ታገሥሁ፥ የፃዕርም ሌሊት ተወሰነችልኝ።
የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል።
ስለዚህ እኔ ደግሞ በክፉ ቍስል መታሁህ፥ ስለ ኃጢአትህም አፈረስሁህ።