ኢዮብ 15:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአሞራዎችም ምግብ ሆኖ ተሰጥቶአል በድን ሆኖ እንደሚቈይም እርሱ ራሱ ያውቃል። የጨለማ ቀንም እንደ አውሎ ነፋስ ትወስደዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሞራ እራት ለመሆን ይቅበዘበዛል፤ የጨለማ ቀን መቅረቡን ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተቅበዝብዞም፦ ወዴት አለ? እያለ እንጀራ ይለምናል፥ የጨለማ ቀን እንደ ቀረበበት ያውቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአሞራ እንደሚጣል ምግብ ይጣላል፤ የሚጠፋበት ጨለማው ቀን እንደ ቀረበበት ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተቅበዝብዞም፦ ወዴት አለ? እያለ እንጀራ ይለምናል፥ የጨለማ ቀን እንደ ቀረበበት ያውቃል። |
ሰው ብዙ ዘመን በሕይወት ቢኖር፥ በሁሉም ደስ ቢለው፤ የጨለማውን ዘመን ያስብ፥ ብዙ ቀን ይሆናልና። የሚመጣውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።
የጨለማና የነፋስ ቀን፥ የደመናና የጉም ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘለዓለምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አልነበረም፤ ከእርሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይሆንም።