ኢዮብ 15:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይልቁንስ አስጸያፊና የረከሰ፥ ኀጢአትንም እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ ክፋትን እንደ ውሃ የሚጠጣ፣ አስጸያፊና ርኩስ ሰውማ እንዴት ይታመን! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ አስጸያፊና የረከሰ፥ በደልን እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?!” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተበላሸና የረከሰ ኃጢአትንም እንደ ውሃ የሚጠጣ ሰውማ ምንኛ የባሰ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይልቁንስ አስጸያፊና የረከሰ፥ ኃጢአትንም እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ? |
ይልቁንም ከአንድ ዐይነት ጭቃ የተፈጠርን እኛ፥ በተፈጠርንበት የጭቃ ቤት የሚኖሩትን እንደ ብል ይጨፈልቃቸዋል።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።