ኢዮብ 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው የሕይወቱን ዘመን ፈጽሞ ከሞተ በኋላ በሕይወት የሚኖር ቢሆን ዳግመኛ እስክወለድ ድረስ፥ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ከሞተ በኋላ ተመልሶ በሕይወት ይኖራል? እድሳቴ እስከሚመጣ ድረስ፣ ተጋድሎ የሞላበትን ዘመኔን ሁሉ እታገሣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን? ዕረፍቴ እስኪመጣ ድረስ፥ የአገልግሎቴን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ከሞተ በኋላ በሕይወተ ሥጋ ሊኖር ይችላልን? ዕረፍቴ እስከምትመጣበት ጊዜ ድረስ፥ ይህን የትግል ዘመኔን ፍጻሜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን? መለወጤ እስኪመጣ ድረስ፥ የሰልፌን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር። |
“በመቃብር ውስጥ ምነው በጠበቅኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪበርድም ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! እስከምታስበኝም ምነው ቀጠሮ በሰጠኸኝ ኖሮ!
በምድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር፤ ወሮቹም በአንተ ዘንድ የተቈጠሩ ናቸው፤ ዘመኑንም ወስነህ ትሰጠዋለህ፤ እርሱም ከዚያ አያልፍም።
ኢዮብም ከደዌው ከዳነ በኋላ መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፥ ኢዮብም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሁለት መቶ አርባ ነው። ልጆቹንና የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ።
እርሱም እንደ ከሃሊነቱ ረዳትነት መጠን የተዋረደውን ሥጋችንን የሚያድሰው፥ ክቡር ሥጋዉንም እንዲመስል የሚያደርገው፥ የሚያስመስለውም፥ ሁሉም የሚገዛለት ነው።