Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ጥን​ቱን በም​ድር ላይ የሰው ሕይ​ወት ጥላ አይ​ደ​ለ​ምን? ኑሮ​ውስ እንደ ቀን ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ተጋድሎ አይደለምን? ዘመኑስ እንደ ምንደኛ ዘመን አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን? ቀኖቹ እንደ ምንደኛ ቀኖች አይደሉምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ሰዎች ሁሉ በምድር ላይ እንደ ግዳጅ ሠራተኞች አይደሉምን? ቀኖቻቸው እንደ ቅጥር ሠራተኞች ቀኖች አይደሉምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን? ወራቱም እንደ ምንደኛ ወራት አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 7:1
16 Referencias Cruzadas  

ዳግ​መ​ኛም ከጥ​ንት ጀምሮ ትመ​ረ​ም​ረ​ኛ​ለህ፤ ታላቅ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመ​ጣ​ህ​ብኝ። ፈተ​ና​ዎ​ች​ንም ላክ​ህ​ብኝ።


“ከሴት የተ​ወ​ለደ ሟች ሰው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን ጥቂት ነው፥ የቍጣ መከ​ራ​ንም የተ​ሞላ ነው።


የአ​ሞራ ግል​ገ​ሎች ግን ወደ ላይ እየ​በ​ረሩ ከፍ እን​ዲሉ፥ ሰው እን​ዲሁ ለድ​ካም ተወ​ል​ዶ​አል።


ወይም ጌታ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈራ አገ​ል​ጋይ ጥላ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​መኝ፥ ወይም ደመ​ወ​ዙን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?


መታ​መ​ኛው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሆነ፥ ወደ ከንቱ ነገር፥ ወደ ቍጣና ወደ ሐሰ​ትም፥ ያል​ተ​መ​ለ​ከተ ሰው ብፁዕ ነው።


መን​ፈ​ስን ለማ​ስ​ቀ​ረት በመ​ን​ፈሱ ላይ ሥል​ጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞ​ትም ቀን ሥል​ጣን የለ​ውም፤ በጦ​ር​ነ​ትም ጊዜ ስን​ብት የለም፥ ኀጢ​አ​ትም ሠሪ​ውን አያ​ድ​ነ​ውም።


አሁ​ንም እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በሦ​ስት ዓመት ውስጥ እንደ ምን​ደኛ ዓመት የሞ​ዓብ ክብር ከብዙ ሀብ​ትዋ ጋር ይዋ​ረ​ዳል፤ በቍ​ጥ​ርም ጥቂት ይቀ​ራል፤ ክብ​ር​ዋም አይ​ገ​ኝም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እን​ዲህ ብሎ​ኛ​ልና፥ “እንደ ምን​ደኛ ዓመት በአ​ንድ ዓመት ውስጥ የቄ​ዳር ልጆች ክብር ሁሉ ይጠ​ፋል፤


“ሂድ፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ በዕ​ድ​ሜህ ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤


ካህ​ናት ሆይ፥ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ልቧ የሚ​ገባ ነገ​ርን ተና​ገሩ፤ ውር​ደቷ እንደ ተፈ​ጸመ፥ ኀጢ​አ​ቷም እንደ ተሰ​ረየ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ስለ ኀጢ​አቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀ​በ​ለች አጽ​ና​ኑ​አት።


ከገ​ዛ​ውም ሰው ጋር ከገ​ዛ​በት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ይቍ​ጠር፤ የሽ​ያ​ጩም ብር እንደ ዓመ​ታቱ ቍጥር ይሁን፤ እንደ ምን​ደ​ኛ​ውም ዘመን ከእ​ርሱ ጋር ይሁን።


እር​ሱ​ንም አር​ነት ባወ​ጣ​ኸው ጊዜ የም​ን​ደ​ኝ​ነ​ቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድ​ርጎ ስድ​ስት ዓመት አገ​ል​ግ​ሎ​ሃ​ልና አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ሠ​ራው ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos