ኢዮብ 13:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአቶችና በደሌ ምን ያህል ናቸው? ምን ያህል እንደ ሆኑ አስታውቀኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደሌና ኀጢአቴ ምን ያህል ነው? መተላለፌንና ኀጢአቴን አስታውቀኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያለብኝስ በደልና ኃጢአት ምን ያህል ነው? መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ የሠራሁት በደልና ኃጢአት ምን ያኽል ነው? እስቲ መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያለብኝስ በደልና ኃጢአት ምን ያህል ነው? መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ። |
ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።”