መከራው ይገባሃል፤ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ ምንድን ነው? ከሰማይ በታች ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ተራራዎች ከመሠረታቸው ይናወጣሉን?
ኢዮብ 13:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፤ ሕይወቴንም በእጄ አጥብቄ አኖራታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋዬን በጥርሴ፣ ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጥርሴን ነክሼ ስጨነቅ የምኖረው ለምንድን ነው? ሕይወቴም በእጄ ላይ ነች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ። |
መከራው ይገባሃል፤ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ ምንድን ነው? ከሰማይ በታች ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ተራራዎች ከመሠረታቸው ይናወጣሉን?
የአስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን ይበላሉ፤ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅም ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መድኀኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብን ኀይል የምደግፍ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
የሚያድን እንደሌለም ባየሁ ጊዜ ሰውነቴን በእጄ አሳልፌ ለሞት በመስጠት ወደ አሞን ልጆች ተሻገርሁ፤ እግዚአብሔርም በፊቴ ጣላቸው፤ ለምንስ ዛሬ ልትወጉኝ ወደ እኔ መጣችሁ?” አላቸው።
ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊዉን ገደለ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ እስራኤልም ሁሉ አይተው ደስ አላቸው፤ በከንቱ ዳዊትን ትገድለው ዘንድ ስለምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ?”
ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጣች፤ እጅግም ደንግጦ እንደ ነበር አይታ፥ “እነሆ፥ እኔ አገልጋይህ ቃልህን ሰማሁ፤ ነፍሴንም በእጄ ጣልሁ፤ የነገርኸኝንም ቃል ሰማሁ።