Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 13:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “ጥርሴን ነክሼ ስጨነቅ የምኖረው ለምንድን ነው? ሕይወቴም በእጄ ላይ ነች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሥጋዬን በጥርሴ፣ ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሥጋ​ዬን በጥ​ርሴ እይ​ዛ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም በእጄ አጥ​ብቄ አኖ​ራ​ታ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 13:14
8 Referencias Cruzadas  

አንተ ብትቈጣ ራስህን ትጐዳለህ እንጂ በአንተ ቊጣ ምድር ባዶ አትሆንም። አለቶችም ከስፍራቸው አይነቃነቁም።


ሕይወቴ በአደጋ ላይ ቢሆንም እንኳ ሕግህን አልረሳም


እጆቹን አጥፎ የሚቀመጥ ሞኝ ሰው ራሱን በራብ ይገድላል።


ጨቋኞችሽ የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰክሩ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ። ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ የእስራኤል ኀያል አምላክ መሆኔን የዓለም ሕዝብ ሁሉ ያውቃል።”


በአንድ በኩል ሆዳቸው እስኪሞላ ይበላሉ፤ ነገር ግን እንደ ተራቡ ናቸው፤ እንዲሁም በሌላ በኩል አግበስብሰው ይውጣሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ የልጆቻቸውን ሥጋ እንኳ እስከ መብላት ይደርሳሉ።


እናንተ እኔን ለመርዳት አለመፈለጋችሁን ባየሁ ጊዜ ለሕይወቴ ሳልሳሳ እነርሱን ለመውጋት ወሰኑን ተሻግሬ ሄድሁ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኝ። ታዲያ፥ አሁን እኔን ለመውጋት የተነሣችሁበት ምክንያት ምንድን ነው?”


እርሱ ለሕይወቱ ሳይሳሳ በመጋፈጥ ጎልያድን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም ይህን ባየህ ጊዜ ደስ ብሎህ ነበር፤ ታዲያ አሁን አንተ በንጹሕ ሰው ላይ በደል ለመሥራት ስለምን ታስባለህ? ምክንያት በሌለውስ ነገር ዳዊትን ለመግደል ስለምን ፈለግኽ?”


ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼአለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos