እግዚአብሔርን የጠራሁ እርሱም የመለሰልኝ እኔ፥ ለባልንጀራው መሣለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፤ ጻድቁና ንጹሑ ሰው መሣለቂያ ሆኖአል።
ኢዮብ 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ በተወሰነው ዕድሜ በሌሎች እንዲወድቅ፥ ቤቱም በኃጥኣን እንዲፈርስ ተዘጋጅቶአል። ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እንደሚሆን አይመን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደላቸው በመከራ ያፌዛሉ፤ እግሩ የተንሸራተተውንም ይገፈትራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተደላድሎ የተቀመጠ ሰው መከራን ይንቃል፥ እግሩን ያዳለጠውንም ለመገፍተር ተዘጋጅቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ችግር ባልደረሰበት ሰው ዘንድ የተቸገረን ሰው ችግር ማናናቅ ቀላል ነው። ነገር ግን ሊወድቅ የሚንገዳገደውን ሰው ትገፈትሩታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተዘልሎ በሚቀመጥ ሰው አሳብ መከራ ይናቃል፥ ነገር ግን እግሩን ሊያድጠው ተዘጋጅቶአል። |
እግዚአብሔርን የጠራሁ እርሱም የመለሰልኝ እኔ፥ ለባልንጀራው መሣለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፤ ጻድቁና ንጹሑ ሰው መሣለቂያ ሆኖአል።
በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው በከንቱ ይጮኻልን? የሚበላውን ፈልጎ አይደለምን? ወይስ በሬ በበረት ውስጥ ገለባ ሳለው ይጮኻልን?
ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።
ሳይጨልምባችሁ፥ ጨለማም ባለባቸው ተራሮች እግሮቻችሁ ሳይሰነካከሉ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፤ በዚያም የሞት ጥላ አለና በጨለማውም ውስጥ ያኖራችኋልና ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ።
ሰውነቴንም እንዲህ እላታለሁ፦ ሰውነቴ ሆይ፥ የሰበሰብሁልሽ ለብዙ ዓመታት የሚበቃሽ የደለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበልሽ።
በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ እግራቸው በሚሰናከልበት ጊዜ፥ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ የተዘጋጀላችሁም ፈጥኖ ይደርስባችኋልና።