La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እርሱ ሁሉን ቢገ​ለ​ብጥ፥ ምን አደ​ረ​ግህ? የሚ​ለው ማን ነው?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እርሱ ተከታትሎ መጥቶ በግዞት ቢያስቀምጥህ፣ የፍርድ ሸንጎም ቢሰበስብ፣ ማን ሊከለክለው ይችላል?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥ የሚከለክለው ማን ነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር መጥቶ ቢያስር፥ ወደ ፍርድ ሸንጎም ቢያቀርብ፥ ማን ይከለክለዋል?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥ የሚከለክለው ማን ነው?

Ver Capítulo



ኢዮብ 11:10
13 Referencias Cruzadas  

ርዝ​መቱ ከም​ድር ይልቅ ይረ​ዝ​ማል፥ ከባ​ሕ​ርም ይልቅ ይሰ​ፋል።


እነሆ፥ እርሱ ቢያ​ፈ​ርስ፥ ማን ይሠ​ራል? በሰ​ውም ላይ ቢዘ​ጋ​በት ማን ይከ​ፍ​ታል?


“እርሱ ዕረ​ፍ​ትን ይሰ​ጣል፤ የሚ​ፈ​ር​ድስ ማን ነው? በሕ​ዝብ ወይም በሰው ዘንድ ፊቱን ቢሰ​ውር የሚ​ያ​የው ማን ነው?


ከእ​ናቷ ማኅ​ፀን በወ​ጣች ጊዜ፥ ባሕ​ርን በመ​ዝ​ጊ​ያ​ዎች ዘጋ​ኋት፤


እርሱ ይሰ​ብ​ራል፥ ዳግ​መ​ኛም ይጠ​ግ​ናል፤ ይቀ​ሥ​ፋል፥ እጆ​ቹም ይፈ​ው​ሳሉ።


በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኀይ​ለ​ኛም፥ ታላ​ቅም ነው፤ ክፉስ ሆኖ በፊቱ የቆመ ማን ነው?


አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ፥ በም​ት​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ አጸ​ና​ሃ​ለሁ። ዐይ​ኖ​ቼን በአ​ንተ ላይ አጸ​ና​ለሁ።


ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን መክ​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር የሚ​መ​ልስ ማን ነው? የተ​ዘ​ረ​ጋች እጁ​ንስ የሚ​መ​ል​ሳት ማን ነው?


በመ​ጀ​መ​ሪያ ለጽ​ዮን፦ ግዛ​ትን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ወደ መን​ገ​ድዋ እመ​ል​ሳ​ታ​ለሁ።


አንዱ ሽሁን እን​ዴት ያሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል? ሁለ​ቱስ ዐሥ​ሩን ሽህ እን​ዴት ያባ​ር​ሩ​አ​ቸ​ዋል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍዳ​ውን አም​ጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና። አም​ላ​ካ​ች​ንም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦