La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 8:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሕ​ዝቤ ሴት ልጅ ስብ​ራት እኔ ወድቄ ተሰ​ብ​ሬ​አ​ለሁ፤ ጠቍ​ሬ​ማ​ለሁ፤ ራስ ማዞ​ርም ይዞ​ኛል፤ ምጥ እን​ደ​ያ​ዛ​ትም ሴት በመ​ከ​ራው እጨ​ነ​ቃ​ለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕዝቤ ሲቈስል፣ እኔም ቈሰልሁ፤ አለቀስሁ፤ ድንጋጤ ያዘኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ ጠቁሬአለሁም፤ ፍርሀትም ይዞኛል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕዝቤ በመሰበሩ የእኔም ልብ ተሰብሮአል፤ ፍርሀትም ይዞኝ አለቅሳለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ ጠቍሬማለሁ፥ አድናቆትም ይዞኛል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 8:21
14 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኑር፤ የአ​ባ​ቶች መቃ​ብር ያለ​ባት ከተማ ተፈ​ት​ታ​ለ​ችና፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና ፊቴ ስለ ምን አያ​ዝን?” አል​ሁት።


“እን​ደ​ዚ​ህም ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የወ​ገኔ ልጅ ድን​ግ​ሊቱ በታ​ላቅ ስብ​ራ​ትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ ሌሊ​ትና ቀን ሳያ​ቋ​ርጡ እን​ባን ያፍ​ስሱ።


ይሁዳ አለ​ቀ​ሰች፤ ደጆ​ች​ዋም ባዶ ሆኑ፤ በም​ድ​ርም ላይ ጨለሙ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎ​አል።


እኔም አን​ተን ተከ​ትዬ አል​ደ​ከ​ም​ሁም፥ የሰ​ው​ንም ቀን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም፤ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ከከ​ን​ፈሬ የወ​ጣ​ውም በፊ​ትህ ነው።


አን​ጀቴ! አን​ጀቴ! ልቤ በጣም ታም​ሞ​አል፤ ነፍ​ሴም አእ​ም​ሮ​ዋን አጥ​ታ​ለች፤ በው​ስ​ጤም ልቤ ታው​ኮ​ብ​ኛል፤ ነፍ​ሴም የመ​ለ​ከ​ትን ድም​ፅና የሰ​ል​ፍን ውካታ ሰም​ታ​ለ​ችና ዝም እል ዘንድ አል​ች​ልም።


መከሩ አል​ፎ​አል፤ በጋ​ውም ዐል​ቋል፤ እኛም አል​ዳ​ን​ንም።


ስለ ተገ​ደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊ​ትና ቀን አለ​ቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐ​ይ​ኔም የዕ​ን​ባን ምንጭ ማን በሰ​ጠኝ?


አሌፍ። በቍ​ጣው በትር ችግር ያየ ሰው እኔ ነኝ።


ከፊ​ታ​ቸው አሕ​ዛብ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ የሰ​ውም ፊት ሁሉ እንደ ድስት ጥላ​ሸት ይጠ​ቍ​ራል።


ባዶና ባድማ ምድረ በዳም ሆናለች፣ ልብ ቀልጦአል፥ ጕልበቶችም ተብረክርከዋል፣ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሰዎችም ሁሉ ፊት ጠቍሮአል።


በደ​ረሰ ጊዜም ከተ​ማ​ዪ​ቱን አይቶ አለ​ቀ​ሰ​ላት።