ዐሥር ጥማድ በሬ ካረሰው የወይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወጣል፤ ስድስት መስፈሪያ የዘራ ሦስት መሥፈሪያ ብቻ ያገባል።
ኤርምያስ 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዝመራቸውን ይሰበስባሉ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ የለም፤ ቅጠልም ይረግፋል፤ ሰጠኋቸው፤ አለፈባቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ያመረቱትን ሁሉ እወስድባቸዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ተክል ላይ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፍ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሎቻቸውም ይረግፋሉ። የሰጠኋቸው በሙሉ፣ ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም፥ ቅጠልም ይረግፋል፤ የሰጠኋቸሁም ይጠፋባቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ገበሬ ሰብሉን እንደሚሰበስብ ሕዝቤን ልሰበስብ ፈለግኹ፤ እነርሱ ግን ዘለላ እንደሌለው የወይን ተክል ፍሬ አልባ እንደ ሆነ የበለስ ዛፍና ቅጠሉ እንደ ረገፈ ተክል ሆኑብኝ፤ በዚህ ምክንያት የሰጠኋቸውን ምድር ባዕዳን እንዲወስዱባቸው አደረግሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም፥ ቅጠልም ይረግፋል፥ የሚያልፉባቸውንም ሰጠኋቸው። |
ዐሥር ጥማድ በሬ ካረሰው የወይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወጣል፤ ስድስት መስፈሪያ የዘራ ሦስት መሥፈሪያ ብቻ ያገባል።
ቢጾሙ ጸሎታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ቢያቀርቡም ደስ አልሰኝባቸውም፤ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ።”
ስለዚህ እግዚአብሔር በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚናገሩ ነቢያት ስላላክኋቸው፦ በዚህች ሀገር ሰይፍና ረሃብ አይሆንም ስለሚሉ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ “እነዚያ ነቢያት በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ።
በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።
መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም፥ ዘይትህንም ይበላሉ፤ የምትታመናቸውን የተመሸጉ ከተሞችህንም በሰይፍ ያጠፋሉ።”
እንግዲህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።”
ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፤ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
እርስዋም፥ “ወዳጆች የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ሁሉ ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ምስክርም ይሆኑ ዘንድ አኖራቸዋለሁ፤ የምድረ በዳም አራዊትና የሰማይ ወፎች፥ የምድር ተንቀሳቃሾችም ይበሉታል።
ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥
እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።
ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፣ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና “ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ፤” አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።
ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።