የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።
ኤርምያስ 52:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በናቡከደነፆር በሃያ ሦስተኛው ዓመተ መንግሥት የአዛዦቹ አለቃ ናቡዛርዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ነፍስ ማርኮአል፤ ሰዎችም ሁሉ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡከደነፆር በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት፣ የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ ሰባት መቶ አርባ ዐምስት አይሁድ ማርኮ ወስዷል። በአጠቃላይ አራት ሺሕ ስድስት መቶ ሰዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ሰው ማርኮ አፈለሰ፤ በአጠቃላይ የሰዎቹ ብዛት አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በነገሠ በሃያ ሦስት ዓመቱ ሰባት መቶ አርባ አምስት አይሁድ በናቡዛርዳን እጅ ተማርከው ተወስደዋል፤ በጠቅላላው ተማርከው የተወሰዱት ሰዎች ቊጥር አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ነፍስ ማርኮአል፥ ሰዎች ሁሉ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። |
የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።
በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ኰብልለውም ወደ እርሱ የገቡትን ሰዎችና የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።
የአዛዦቹም አለቃ ናቡዛርዳን የሕዝቡን ድኆች፥ በከተማም ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የሕዝቡንም ቅሬታ አመጣ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ወይንን እንደሚቃርም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን ይቃርሙአቸዋል፤ እጅህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እንቅብ ዘርጋ።