በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ ፈርዖን ኒካዑ በኤማት ምድር ባለችው በዴብላታ አሰረው፤ በምድሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መቶ መክሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለበት።
ኤርምያስ 52:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዛዦቹም አለቃ ናቡዛርዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ዴብላታ ወሰዳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ናቡዘረዳን እነዚህን ሁሉ ይዞ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ነበረበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡዛርዳን እነዚህን ሁሉ በሐማት ግዛት ውስጥ በሪብላ ከተማ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወሰዳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። |
በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ ፈርዖን ኒካዑ በኤማት ምድር ባለችው በዴብላታ አሰረው፤ በምድሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መቶ መክሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለበት።
በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
የከለዳውያንም ሠራዊት ተከታተላቸው፤ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ ሜዳ አገኙት፤ ይዘውም በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ዴብላታ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።
የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ኰብልለውም ወደ እርሱ የገቡትን ሰዎችና የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።
ዳርቻውም ከሴፋማ በዐይን ምሥራቅ ወዳለው ወደ አርቤላ ይወርዳል፤ እስከ ኬኔሬት የባሕር ወሽመጥ በምሥራቅ በኩል ይደርሳል፤