La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 52:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የና​ሱም ጕል​ላት በላዩ ነበረ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው ሁሉ ከናስ የተ​ሠሩ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዐምድ ደግሞ እን​ደ​ዚህ ያለ ነገ​ርና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአንዱ ዐምድ ዐናት ላይ ያለው የናስ ጕልላት ቁመት ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ዙሪያውንም ሁሉ የሮማን ቅርጽ ባላቸው የናስ ጌጣጌጦች የተዋበ ነበር፤ ሌላውም ዐምድ የሮማኑን ጌጣጌጥ ጨምሮ ከዚሁ ጋራ ተመሳሳይ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የናሱም ጉልላት በላዩ ነበረ፤ የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፥ በጉልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት፤ በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእያንዳንዱም ምሰሶ ጒልላት ከነሐስ የተሠራ ሆኖ ሁለት ሜትር ያኽል ከፍታ የነበረውና በመረብና በሮማን ፍሬ ቅርጽ የተጌጠ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የናሱም ጕልላት በላዩ ነበረ፥ የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፥ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት፥ በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 52:22
9 Referencias Cruzadas  

በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ በነ​በ​ሩት ጕል​ላ​ቶች ላይ በመ​ር​በቡ ሥራ አጠ​ገብ ሮማ​ኖ​ቹን አደ​ረገ። ሮማ​ኖ​ቹም በአ​ንዱ ወገን ሁለት መቶ ነበሩ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ጕል​ላት እን​ዲሁ ነበረ።


በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች ይሸ​ፍኑ ዘንድ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መር​በብ በሁ​ለት በሁ​ለት ተራ አድ​ርጎ ለሁ​ለቱ መር​በ​ቦች አራት መቶ ሮማ​ኖ​ችን አደ​ረገ።


የአ​ን​ዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፥ የና​ስም ጕል​ላት ነበ​ረ​በት፤ የጕ​ል​ላ​ቱም ርዝ​መት ሦስት ክንድ ነበረ፥ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው የናስ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበሩ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓምድ ላይ መር​በብ ነበ​ረ​በት።


በቤ​ቱም ፊት ቁመ​ታ​ቸው ሠላሳ አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች ሠራ፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ላይ የነ​በ​ረው ጕል​ላት አም​ስት ክንድ ነበረ።


የሁ​ለ​ቱ​ንም ቋዶች ጫፎች በሁ​ለቱ ፈር​ጦች ውስጥ አግ​ብ​ተህ በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ በስ​ተ​ፊት በመ​ጋ​ጠ​ሚ​ያ​ቸው ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።