ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በመዓት እጐበኛቸዋለሁ፤ ጐበዛዝቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤
ኤርምያስ 49:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ጐበዛዝቷ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፤ በዚያም ቀን ሰልፈኞች ሁሉ ይወድቃሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ወንዶች ወጣቶቿ በየአደባባዩ ይረግፋሉ፤ በዚያ ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይወድቃሉ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጐልማሶችዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፥ በዚያም ቀን ወታደሮችዋ ሁሉ ይጠፋሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን የዚያች ከተማ ወጣቶች በከተማይቱ መንገዶች ላይ ይገደላሉ፤ ወታደሮችዋም ይደመሰሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፥ በዚያም ቀን ሰልፈኞች ሁሉ ይጠፋሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በመዓት እጐበኛቸዋለሁ፤ ጐበዛዝቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤
ሕፃናቱንም በመንገድ፤ ጐልማሶቹንም በአደባባዮቻችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመስኮቶቻችን ወደ ሀገራችን ገብቶአልና።
ሣን። ብላቴናውና ሽማግሌው በመንገዶች ላይ ተጋደሙ፤ ደናግሎችና ጐልማሶች ተማርከዋል፤ በሰይፍም ወድቀዋል፤ በረኃብ ገደልሃቸው፤ በቍጣህም ቀን ሳትራራ አረድሃቸው።
ኀይልሽና ዋጋሽ፥ ንግድሽም፥ መርከበኞችሽም፥ መርከብ መሪዎችሽም፥ ሰባራሽን የሚጠግኑ ነጋዴዎችሽም፥ በአንቺም ዘንድ ያሉ ሰልፈኞችሽ ሁሉ በውስጥሽ ከአሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በወደቅሽበት ቀን በባሕር ውስጥ ይጠፋሉ።
“በግብፅ እንደ ሆነው ሞትን ሰደድሁባችሁ፤ ጐበዛዝቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፤ በሰፈራችሁም እሳትን ሰድጄ አጠፋኋችሁ፤ በዚህም ሁሉ እናንተ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።