ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፥ “ራስህን አድን፤ ወደ ኋላም አትመልከት፤ አንተንም መከራ እንዳታገኝህ በዚች ሀገር በዳርቻዋና በተራራዋ አትቁም።”
ኤርምያስ 48:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሸሽታችሁ ራሳችሁን አድኑ፤ እንደ ሜዳ አህያ በምድረ በዳ ተቀመጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽሹ፤ ሕይወታችሁንም አትርፉ! በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሸሽታችሁ ራሳችሁን አድኑ፤ በምድረ በዳ እንዳለ ቁጥቋጦ ሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስ በርሳቸውም ‘ሕይወታችሁን ለማትረፍ በፍጥነት ሩጡ! በበረሓም እንደሚኖር የሜዳ አህያ ብረሩ!’ ይባባላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሸሽታችሁ ራሳችሁን አድኑ፥ በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ሁኑ። |
ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፥ “ራስህን አድን፤ ወደ ኋላም አትመልከት፤ አንተንም መከራ እንዳታገኝህ በዚች ሀገር በዳርቻዋና በተራራዋ አትቁም።”
በምድረ በዳ እንደ አለ ቍጥቋጦ ይሆናል፤ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በማይኖርበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደረቅ ስፍራ ይቀመጣል።
ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፤ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራቷን ይከፍላታልና።
ዮሐንስም ሊያጠምቃቸው የመጡትን ሰዎች እንዲህ አላቸው፥ “እናንት የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው መቅሠፍት ታመልጡ ዘንድ ማን ነገራችሁ?
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።