ያንጊዜም ሰሎሞን ለሞአብ ርኵሰት ለኮሞስ፥ ለአሞን ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም አንጻር በአለው ተራራ ላይ መስገጃን ሠራ።
ኤርምያስ 48:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞአብ ሆይ! ወዮልሽ! የካሞሸ ወገን ጠፍቶአል፤ ወንዶች ልጆችሽ ተማርከው ተወስደዋልና፥ ሴቶች ልጆችሽም ወደ ምርኮ ሄደዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ተደምስሷል፤ ወንዶች ልጆችህ በምርኮ ተወስደዋል፤ ሴቶች ልጆችህም ተግዘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞዓብ ሆይ! ወዮልህ! የካሞሽ ሰዎች ጠፍቶአል፤ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፥ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሞአብ ሕዝብ ወዮላችሁ! ካሞሽ ለተባለው ጣዖት የሚሰግዱ ሕዝብ ተደመሰሱ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም ተማርከው ተወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የካሞሽ ወገን ጠፍቶአል፥ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፥ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና። |
ያንጊዜም ሰሎሞን ለሞአብ ርኵሰት ለኮሞስ፥ ለአሞን ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም አንጻር በአለው ተራራ ላይ መስገጃን ሠራ።
በኢየሩሳሌምም ፊት ለፊት በርኵስት ተራራ ቀኝ የነበሩትን፥ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን ርኵስት ለአስታሮት፥ ለሞዓብም ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ ያሠራቸውን መስገጃዎች ንጉሡ ርኩስ አደረገ።
በሥራሽና በመዝገብሽ ታምነሻልና አንቺ ደግሞ ትያዢያለሽ፤ ካሞሽም ከካህናቱና ከአለቆቹ ጋር በአንድነት ይማረካል።
ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የካሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቻቸውን ለማደን፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለምርኮ፤ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ።
አምላክህ ኮሞስ የሚሰጥህን የምትወርስ አይደለህምን? እኛም አምላካችን እግዚአብሔር ከፊታችን ያስወጣቸውን የእነርሱን ምድር የምንወርስ አይደለንምን?