ኤርምያስ 48:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሞአብ የምትኖር ሆይ! ፍርሀትና ጕድጓድ፥ ወጥመድም በአንተ ላይ አሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞዓብ ሕዝብ ሆይ፤ ሽብርና ጕድጓድ፣ ወጥመድም ይጠብቅሃል፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞዓብ የምትኖር ሆይ! ፍርሃትና ጉድጓድ ወጥመድም በአንተ ላይ አለ፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞአብ ሕዝብ ሆይ፥ “ሽብር፥ የሚያሰናክል ጒድጓድና ወጥመድ ይጠብቃችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሞዓብ የምትኖር ሆይ፥ ፍርሃትና ጕድጓድ ወጥመድም በአንተ ላይ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እነሆ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍርሀትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፤ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም።
ባቢሎን ሆይ! በመከራው ተይዘሽ ጠፋሽ፤ አንቺም ይህ እንደመጣብሽ አላወቅሽም፤ እግዚአብሔርን ተቃውመሽዋልና ተገኝተሻል፤ ተይዘሽማል።