ኤርምያስ 48:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞአብም በእግዚአብሔር ላይ ኰርታለችና ሕዝብ ከመሆን ትጠፋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞዓብ እግዚአብሔርን አቃልሏልና ይጠፋል፤ መንግሥትነቱም ይቀራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞዓብም በጌታ ላይ ኰርቶአልና ከእንግዲህ ወድያ ሕዝብ አይሆንም፥ እርሱም ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞአብ በእኔ ላይ ስለ ታበየች ትደመሰሳለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ በመንግሥትነት አትታወቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓብም በእግዚአብሔር ላይ ኰርቶአልና ሕዝብ ከመሆን ይጠፋል። |
አሁንም እንዲህ እላለሁ፤ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብር ከብዙ ሀብትዋ ጋር ይዋረዳል፤ በቍጥርም ጥቂት ይቀራል፤ ክብርዋም አይገኝም።
የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማንን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግህበት፥ ዐይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን?
የአራም ራስ ደማስቆ ነው፤ የደማስቆም ራስ ረአሶን ነው፤ በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ የኤፍሬም መንግሥት ከሕዝብ ይጠፋል፤
አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥” ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም።”
ከእንግዲህ ወዲህ የሞአብ ፈውስ የለም፤ በሐሴቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት” ብለው ክፉ ነገርን አስበውባታል። ፈጽሞ ትተዋለች፤ ከኋላዋ ሰይፍ ይመጣልና።
“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።