ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
ኤርምያስ 48:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤሊያሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፤ ከሴጎር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፤ የኔምሬም ውኃ ደርቋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣ ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣ ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤ የኔምሬም ውሃ እንኳ ደርቋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሐሴቦን ጮኹ እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን አሰሙ፤ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ደርሶአል፤ የኔምሬም ውኃ ደግሞ ይደርቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሐሴቦንና የዔልዓሌ ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ጩኸታቸውም እስከ ያሀጽ ተሰምቶአል፤ ከጾዓር እስከ ሖሮናይምና ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ተሰምቶአል፤ የኒምሪም ውሃ እንኳ ደርቆአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፥ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፥ የኔምሬም ውኃ ደግሞ ይደርቃል። |
ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
ከሰዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ከበርሳ፥ ከአዳማ ንጉሥ ከሰናአር፥ ከሲባዮ ንጉሥ ከሲምቦር፤ ሴጎር ከተባለች ከባላ ንጉሥም ጋር ጦርነት አደረጉ።