ዐሥር ጥማድ በሬ ካረሰው የወይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወጣል፤ ስድስት መስፈሪያ የዘራ ሦስት መሥፈሪያ ብቻ ያገባል።
ኤርምያስ 48:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞአብ ምድር ጠፍተዋል፤ ወይን ከመጥመቂያው ጠፍቶአል፤ በነግህ የሚጠምቁት የለም፤ በሠርክም የሚያደርጉት የእልልታ ድምፅ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሞዓብ የአትክልት ቦታና ዕርሻ፣ ሐሤትና ደስታ ርቋል፤ የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤ በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤ በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣ የእልልታ ድምፅ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፤ የወይ ጠጁን ከወይን መጥመቂያው አጥፍቻለሁ፤ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደስታና ሐሴት ለምለም ከሆነችው ከሞአብ ምድር ተወስደዋል፤ ከወይን መጭመቂያዎች ሁሉ የወይን ጠጅ እንዳይፈስስ አድርጌአለሁ፤ የደስታ ድምፅ እያሰማ የሚጨምቅ የለም፤ ድምፅ የሚሰማ ቢሆንም የሚሰማው ድምፅ ግን የደስታ ድምፅ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፥ ጠጁን ከመጥመቂያው አጥፍቻለሁ፥ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም። |
ዐሥር ጥማድ በሬ ካረሰው የወይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወጣል፤ ስድስት መስፈሪያ የዘራ ሦስት መሥፈሪያ ብቻ ያገባል።
በዚያም ወራት እንዲህ ይሆናል፤ ወይን በሀገሩ ሁሉ የበጀ ይሆናል፤ የአንድ ሺህ የወይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆናል። ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ እሾህንና ኵርንችትንም ትሞላለች፤ ፍርሀትም ይመጣል።
እናንተ ሰካራሞች፥ ንቁ፤ ለመስከርም ወይንን የምትጠጡ እናንተ ሁላችሁ! ተድላና ደስታ ከአፋችሁ ጠፍትዋልና አልቅሱ፤ እዘኑም።
በዚያን ዘመን ሁሉ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፣ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው ሀያ ብቻ ነው።