ከተሞቻቸውንም አፈረሱ፤ በመልካሞቹም እርሻዎቻቸው ሁሉ ላይ እስኪሞሉ ድረስ እያንዳንዱ ሰው አንድ አንድ ድንጋይ ይጥል ነበር፤ የውኃውንም ምንጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከተሞቻቸውንም ቅጥር አፈረሱ፤ የሚያምሩትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወንጭፎችም ከብበው መቱአቸው።
ኤርምያስ 48:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰለዚህ ለሞአብ አለቅሳለሁ፤ ለሞአብም ሁሉ እጮኻለሁ፤ ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤ ለሞዓብ ምድር ሁሉ ዋይ እላለሁ፤ ለቂርሔሬስ ሰዎችም የልቅሶ ድምፅ አሰማለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ ለሞዓብም ሁሉ እጮኻለሁ፤ ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሞአብ ዋይ፥ ዋይ እልላታለሁ፤ ለሞአባውያን ሁሉ ድምፄን ከፍ ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፥ ለቂርሔሬስ ሰዎች የሐዘን ለቅሶ አለቅሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ ለሞዓብም ሁሉ እጮኻለሁ፥ ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ። |
ከተሞቻቸውንም አፈረሱ፤ በመልካሞቹም እርሻዎቻቸው ሁሉ ላይ እስኪሞሉ ድረስ እያንዳንዱ ሰው አንድ አንድ ድንጋይ ይጥል ነበር፤ የውኃውንም ምንጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከተሞቻቸውንም ቅጥር አፈረሱ፤ የሚያምሩትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወንጭፎችም ከብበው መቱአቸው።
ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮኻለች፤ ለልቧም ይረዳታል፤ እስከ ሴጎርም ድረስ ብቻዋን ታለቅሳለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉሒት ዐቀበት ትጮኻለች። በአሮሜዎን መንገድም ይመለሳሉ፤ ይጮኻሉም፥ ጥፋትና መናወጥም ይሆናል።
“ያተረፈው ትርፉ ጠፍቶበታልና ስለዚህ ልቤ ለሞአብ እንደ እንቢልታ ይጮኻል፤ ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ይጮኻል፤