Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 48:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 “ያተ​ረ​ፈው ትርፉ ጠፍ​ቶ​በ​ታ​ልና ስለ​ዚህ ልቤ ለሞ​አብ እንደ እን​ቢ​ልታ ይጮ​ኻል፤ ልቤም ለቂ​ር​ሔ​ሬስ ሰዎች እንደ እን​ቢ​ልታ ይጮ​ኻል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 “ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት ያንጐራጕራል፤ ለቂርሔሬስ ሰዎችም እንደ ዋሽንት ያንጐራጕራል። ያከማቹት ንብረት ጠፍቷልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ያተረፈው ትርፉ ጠፍቶበታልና፤ ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ እንቢልታ ድምፅ ይቃትታል፥ ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ድምፅ ይቃትታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 “በሞአብና በቂርሔሬስ የሚኖሩ ሕዝብ የነበራቸውን ሁሉ በማጣታቸው ምክንያት በዋሽንት ተመርተው እንደሚያለቅሱ ሰዎች አለቅስላቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ያተረፈው ትርፉ ጠፍቶበታልና፥ ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ እንቢልታ ይጮኻል፥ ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ይጮኻል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 48:36
14 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ ሞዓብ ይድ​ና​ልን? ዐረ​ባ​ው​ያ​ንን ወደ ሸለ​ቆው አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ስ​ዷ​ታል።


ስለ​ዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ እንደ መሰ​ንቆ ትጮ​ኻ​ለች። አጥ​ን​ቶ​ችም እንደ ተመ​ረገ ግድ​ግዳ ይሆ​ናሉ።


ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮ​ኻ​ለች፤ ለል​ቧም ይረ​ዳ​ታል፤ እስከ ሴጎ​ርም ድረስ ብቻ​ዋን ታለ​ቅ​ሳ​ለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉ​ሒት ዐቀ​በት ትጮ​ኻ​ለች። በአ​ሮ​ሜ​ዎን መን​ገ​ድም ይመ​ለ​ሳሉ፤ ይጮ​ኻ​ሉም፥ ጥፋ​ትና መና​ወ​ጥም ይሆ​ናል።


ቆቅ ጮኸች፤ ያል​ወ​ለ​ደ​ች​ው​ንም ዐቀ​ፈች፤ በዐ​መፅ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትን የሚ​ሰ​በ​ስብ ሰውም እን​ደ​ዚሁ ነው፤ በእ​ኩ​ሌታ ዘመኑ ይተ​ወ​ዋል፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውም ሰነፍ ይሆ​ናል።


አን​ጀቴ! አን​ጀቴ! ልቤ በጣም ታም​ሞ​አል፤ ነፍ​ሴም አእ​ም​ሮ​ዋን አጥ​ታ​ለች፤ በው​ስ​ጤም ልቤ ታው​ኮ​ብ​ኛል፤ ነፍ​ሴም የመ​ለ​ከ​ትን ድም​ፅና የሰ​ል​ፍን ውካታ ሰም​ታ​ለ​ችና ዝም እል ዘንድ አል​ች​ልም።


ከሰ​ማይ ተመ​ለስ፤ ከቅ​ድ​ስ​ና​ህና ከክ​ብ​ርህ ማደ​ሪ​ያም ተመ​ል​ከት፤ ቅን​አ​ት​ህና ኀይ​ል​ህስ ወዴት ነው? የቸ​ር​ነ​ት​ህና የይ​ቅ​ር​ታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለ​ሃ​ልና።


የባለጠጋ ሰው ሀብቱ የጸናች ከተማ ናት፥ ክብሯም እንደ ትልቅ ጥላ ታጠላለች።


ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።


በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።


ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረሱ፤ በመ​ል​ካ​ሞ​ቹም እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ እስ​ኪ​ሞሉ ድረስ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው አንድ አንድ ድን​ጋይ ይጥል ነበር፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቅጥር አፈ​ረሱ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወን​ጭ​ፎ​ችም ከብ​በው መቱ​አ​ቸው።


ሰለ​ዚህ ለሞ​አብ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ለሞ​አ​ብም ሁሉ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ለቂ​ር​ሔ​ሬስ ሰዎች አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios