ኤርምያስ 48:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣ ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠችውን፦ ምን ሆኖአል?፥ ብለሽ ጠይቂ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓሮዔር የምትኖሩ ሁሉ፥ በመንገድ ዳር ቆማችሁ ተጠባበቁ፤ የሚሸሹትን ወንዶችና የሚያመልጡትን ሴቶች ሁሉ በመጠየቅ፥ የሆነውን ነገር ሁሉ ዕወቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፥ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፥ የሸሸውንና ያመለጠችውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂ። |
በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ተራራ ድረስ ማንኛዪቱም ከተማ አላመለጠችንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን።
በሐሴቦን የተቀመጠው፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ኢያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤
እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አላዳንሃቸውም ነበር?
ሰውዬውንም፥ “አንተ ከወዴት ነህ?” አለው። እርሱም፥ “ጦርነቱ ከአለበት ስፍራ የመጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰልፍ ሸሸሁ” አለ። እርሱም፥ “ልጄ ሆይ! ነገሩስ እንዴት ሆነ?” አለው።