እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወንዞች መካከል የሚተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራሴም ሠርቼዋለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ! እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።
ኤርምያስ 46:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግብፅ እንደ ወንዝ ይነሣል፤ ከባሕሩም እንደሚታወክ ማዕበል ይሆናል፤ እርሱም እንዲህ ብሏል፥ “እነሣለሁ፤ ምድርንም ሁሉ እከድናለሁ፤ ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብጽ እንደ አባይ ወንዝ ሙላት ይዘልላል፤ እንደ ደራሽ ወንዝ ይወረወራል፤ ‘እወጣለሁ፤ ምድርንም እሸፍናለሁ፤ ከተሞችንና ነዋሪዎቻቸውን አጠፋለሁ’ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግብጽ እንደ ግብጽ ወንዝ ይነሳል ውኃውም እንደ ወንዞች ይናወጣል፤ እርሱም፦ እነሣለሁ ምድርንም ሁሉ እሸፍናለሁ፤ ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ ብሏል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ዓባይ ወንዝ የተነሣችውና ሞልቶ በጐርፉ ዳርቻውን ሁሉ እንደሚያጥለቀልቅ ወንዝ የሆነችው ግብጽ ነች፤ ግብጽ እንዲህ ብላለች ‘እኔ ተነሥቼ ዓለምን አጥለቀልቃለሁ። ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን ሕዝብ ሁሉ እደመስሳለሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግብጽ እንደ ግብጽ ወንዝ ይነሳል ውኃውም እንደ ወንዙ ይናወጣል፥ እርሱም፦ እነሣለሁ ምድርንም ሁሉ እከድናለሁ፥ ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ ብሎአል። |
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወንዞች መካከል የሚተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራሴም ሠርቼዋለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ! እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፤ እንዲህም በለው፦ የአሕዛብን አንበሳ መስለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነሃል፤ ወንዞችህንም ወግተሃል፤ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም በተረከዝህ ረግጠሃል።
በውኑ ምድሪቱ ስለዚህ ነገር አትናወጥምን? በእርስዋም የሚኖር ሁሉ አያለቅስምን? ጦርነት እንደ ወንዝ ይፈስሳል፤ እንደ ግብፅም ወንዝ ይሞላል፤ ደግሞም ይወርዳል።